Ezra 2

ወደ አገራቸው የተመለሱ ምርኮኞች ዝርዝር

2፥1-70 ተጓ ምብ – ነህ 7፥6-73 1የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን ማርኮ ከወሰዳቸው መካከል ከምርኮ ተመልሰው ወደ የራሳቸው ከተሞች፣ ወደ ይሁዳና ወደ ኢየሩሳሌም የመጡት የአገሩ ልጆች እነዚህ ናቸው፤
2
In order to format the table contained in this verse correctly, it has been necessary to move the content of some adjacent verses into it.
የመጡትም ከዘሩባቤል፣ ከኢያሱ፣ ከነህምያ፣ ከሠራያ፣ ከረዕላያ፣ ከመርዶክዮስ፣ ከበላሳን፣ ከመሴፋር፣ ከበጉዋይ፣ ከሬሁም፣ ከበዓና ጋር ነበር።

የተመለሱት የእስራኤል ሰዎች ዝርዝር የሚከተለው ነው፦
 3የፋሮስ ዘሮች 2,172
 4የሰፋጥያስ ዘሮች 372
 5የኤራ ዘሮች 775
 6ከኢያሱና ከኢዮአብ ዘር የሆኑት የፈሐት ሞዓብ ዘሮች 2,812
 7የኤላም ዘሮች 1,254
 8የዛቱዕ ዘሮች 945
 9የዘካይ ዘሮች 760
 10የባኒ ዘሮች 642
 11የቤባይ ዘሮች 623
 12የዓዝጋድ ዘሮች 1,222
 13የአዶኒቃም ዘሮች 666
 14የበጉዋይ ዘሮች 2,056
 15የዓዲን ዘሮች 454
 16የሕዝቅያስ ልጅ የአጤር ዘሮች 98
 17የቤሳይ ዘሮች 323
 18የዮራ ዘሮች 112
 19የሐሱም ዘሮች 223
 20የጋቤር ዘሮች 95
 21የቤተ ልሔም ሰዎች
ወይም ልጆች፣ ዘሮች
123
 22የነጦፋ ሰዎች 56
 23የዓናቶት ሰዎች 128
 24የዓዝሞት ዘሮች 42
 25የቂርያትይዓሪም
የሰብዓ ሊቃናት ትርጕም (እንዲሁም ነህ 7፥29 ይመ)፤ ዕብራይስጡ ግን፣ ቂሪያት ኦሪም ይላል።
፣ የከፊራና የብኤሮት ዘሮች
743
 26የራማና የጌባ ዘሮች 621
 27የማክማስ ሰዎች 122
 28የቤቴልና የጋይ ሰዎች 223
 29የናባው ዘሮች 52
 30የመጌብስ ዘሮች 156
 31የሌላው ኤላም ዘሮች 1,254
 32የካሪም ዘሮች 320
 33የሎድ፣ የሐዲድና 725
 34የኢያሪኮ ሰዎች 345
 35የሴናዓ ዘሮች 3,630

36
In order to format the table contained in this verse correctly, it has been necessary to move the content of some adjacent verses into it.
ካህናቱ፦
ከኢያሱ ቤተ ሰብ የዮዳኤ ዘሮች 973
 37የኢሜር ዘሮች 1,052
 38የፋስኮር ዘሮች 1,247
 39የካሪም ዘሮች 1,017

40ሌዋውያኑ፦

በሆዳይዋ በኩል የኢያሱና የቀድምኤል ዘሮች     74

41መዘምራኑ፦

የአሳፍ ዘሮች     128

42የቤተ መቅደሱ በረኞች፦

የሰሎም፣ የአጤር፣ የጤልሞን፣ የዓቁብ፣ የሐጢጣና የሶባይ ዘሮች     139

43
In order to format the table contained in this verse correctly, it has been necessary to move the content of some adjacent verses into it.
የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች፦
የሲሐ፣ የሐሡፋና የጠብዖት ዘሮች፤
 44የኬራስ፣ የሲዓ፣ የፋዶን ዘሮች፤
 45የልባና፣ የአጋባ፣ የዓቁብ ዘሮች፤
 46የአጋብ፣ የሰምላይ፣ የሐናን ዘሮች፤
 47የጌዴል፣ የጋሐር፣ የራያ ዘሮች፤
 48የረአሶን፣ የኔቆዳ፣ የጋሴም ዘሮች፤
 49የዖዛ፣ የፋሴሐ፣ የቤሳይ ዘሮች፤
 50የአስና፣ የምዑናውያን፣ የንፉሰሲም ዘሮች፤
 51የበቅቡቅ፣ የሐቁፋ፣ የሐርሑር ዘሮች፤
 52የበስሎት፣ የምሒዳ፣ የሐርሳ ዘሮች፤
 53የበርቆስ፣ የሲሣራ፣ የቴማ ዘሮች፤
 54የንስያና የሐጢፋ ዘሮች።

55
In order to format the table contained in this verse correctly, it has been necessary to move the content of some adjacent verses into it.
የሰሎሞን አገልጋዮች ዘሮች፦
የሶጣይ፣ የሶፌሬት፣ የፍሩዳ ዘሮች፤
 56የየዕላ፣ የደርቆን፣ የጌዴል ዘሮች፤
 57የሰፋጥያስ፣ የሐጢል፣
የፈክራት ሐፂቦይም፣ የአሚ ዘሮች፤
 58የቤተ መቅደሱ አገልጋዮችና የሰሎሞን አገልጋዮች ዘሮች 392

59
In order to format the table contained in this verse correctly, it has been necessary to move the content of some adjacent verses into it.
ከዚህ የሚከተሉት ደግሞ ከቴልሜላ፣ ከቴላሬሳ፣ ከክሩብ፣ ከአዳንና ከኢሜር ከተሞች የመጡ ናቸው፤ ነገር ግን ቤተ ሰቦቻቸው የእስራኤል ዘር መሆናቸውን ማስረዳት አልቻሉም፦
 60የዳላያ፣ የጦብያና የኔቆዳ ዘሮች 652

61ከካህናቱ መካከል፦
የኤብያ፣ የአቆስና የቤርዜሊ ዘሮች፤ ቤርዜሊ በዚህ ስም ሊጠራ የቻለው የገለዓዳዊውን የቤርዜሊን ልጅ አግብቶ ስለ ነበር ነው።
62እነዚህ በትውልድ መዝገቡ ውስጥ የቤተ ሰባቸውን ዝርዝር ፈለጉ፤ ነገር ግን ማግኘት አልቻሉም፤ ስለዚህ እንዳልነጹ ተቈጥረው፣ ከክህነት አገልግሎት ተገለሉ። 63አገረ ገዥውም በኡሪምና በቱሚም እግዚአብሔርን የሚጠይቅ ካህን እስኪነሣ ድረስ፣ እጅግ ከተቀደሰው ምግብ እንዳይበሉ አዘዛቸው።

64ከምርኮ የተመለሱት ሰዎች ብዛት 42,360 ነበረ፤ 65ይህም 7,337 ከሚሆኑት ከወንዶችና ከሴቶች አገልጋዮቻቸው በተጨማሪ ነው፤ 200 ወንድና ሴት ዘማሪዎችም ነበሯቸው። 66736 ፈረሶች፣ 245 በቅሎዎች፣ 67435 ግመሎችና 6,720 አህዮች ነበሯቸው።

68በኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ወደ እግዚአብሔር ቤት በደረሱ ጊዜ፣ አንዳንድ የቤተ ሰብ መሪዎች በቀድሞው ቦታ እንደ ገና ለሚሠራው የእግዚአብሔር ቤት በበጎ ፈቃድ ስጦታ አደረጉ። 69እንደየችሎታቸውም 61,000 የወርቅ ዳሪክ
500 ኪሎ ግራም ያህል ነው።
፣ 5,000 ምናን
2.9 ሜትሪክ ቶን ያህል ነው።
ብር፣ 100 ልብሰ ተክህኖ ለግምጃ ቤቱ ሰጡ።

70ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ፣ መዘምራኑ፣ በር ጠባቂዎቹና የቤተ መቅደስ አገልጋዮቹ፣ ከሌሎች ሰዎች ጋር በየራሳቸው ከተሞች ሰፈሩ፤ የቀሩት እስራኤላውያንም በየከተሞቻቸው ተቀመጡ።

Copyright information for AmhNASV